
ባሕር ዳር: ጥር 10/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የተወዳጁ አርቲስት ነፃነት ወርቅነህ ሥርዓተ ቀብር በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈፅሟል።
ከሥርዓተ ቀብሩ አስቀድሞ በተካሄደው የአስከሬን ሽኝት ሥነ-ሥርዓተ ላይ የአርቲስቱ ወዳጆች፣ የሥራ ባልደረቦች፣ የሙያ አጋሮች እና አድናቂዎች የአበባ ጉንጉን ማስቀመጣቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።
አርቲስት ነፃነት በነበረው ጥልቅ የጥበብ ፍቅር ከ16 ዓመቱ ጀምሮ በርካታ የሬድዮ ድራማዎች፣ ፊልሞች እና ቴአትሮች ደራሲና አዘጋጅ ኾኖ ሰርቷል።
ነፃነት የጤና እክል ገጥሞት በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ ጥር 8 ቀን 2018 ዓ.ም በተወለደ 44 ዓመቱ በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ይታወቃል።
አርቲስቱ ለተቸገሩ ሰዎች ደራሽ፣ የተረሱትን አስታዋሽ፣ ደግና የዋህ ሰው እንደነበር የሚያውቁት ይመሰክራሉ።
በጥበብ ሥራዎቹ ተወዳጅ የሆነው አርቲስት ነፃነት ባለትዳርና የ3 ልጆች አባት ነበር።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
