
ባሕር ዳር: ጥር 10/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ከትናንት በስቲያ ድንገተኛ ህልፈቱ የተሰማው ተወዳጁ የኪነ-ጥበብ ባለሙያ ነጻነት ወርቅነህ የአስከሬን ሽኝት ሥነ-ሥርዓት በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እየተካሄደ መኾኑን ከኢቢሲ ዶት ስትሪም ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
በፊልም እና ቴአትር ተዋናይነት፣ በቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢነት እና በሌሎች የጥበብ ሥራዎቹ ስመጥር እና ተወዳጅ የሆነው ነጻነት ወርቅነህ ባደረበት ሕመም ጥር 8 ቀን 2018 ዓ.ም በድንገት ሕይዎቱ ማለፉ ይታወሳል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
