ደንቢ ኢኮ ሎጅ ተመረቀ።

26
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የገበታ ለትውልድ ሥራ የመጀመሪያው መዳረሻ የሆነው እና በ36 ነጥብ 7 ሄክታር የጥብቅ ደን እና የተፈጥሮ ሃብት ስጦታ የተዘረጋው ደንቢ ኢኮ ሎጅ በይፋ ተመርቋል።
ኢኮ ሎጁ የሀገራችን የቱሪዝም ዘርፍ ባለፉት ሰባት ዓመታት ዘላቂነትን፣ የቅርስ ሃብትን እና ለዘመናት የሚዘልቅ ዓለምአቀፍ ደረጃን የመጠበቅ ዕድል መፍጠርን በማዋሃድ ምን ያህል እንደተለወጠ ማሳያ ነው።
የገበታ ለትውልድ ሥራ ዓለምአቀፍ ደረጃን የጠበቁ መዳረሻዎችን በማልማት የሀገራችንን እምቅ አቅም ለማውጣት የሚደረገው የሰፊው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ስትራቴጂ አካል ነው።
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የተጀመረው ይኽ ሥራ በስኬት ከተተገበሩት የገበታ ለሸገር እና ገበታ ለሀገር መርሐ ግብሮች የቀጠለ እና ሥራዎቹን ወደ አዳዲስ አካባቢዎች የወሰደ ሲሆን የተፈጥሮ ውበትን፣ የባሕል ቅርስን እና ዘላቂ ልምድን በማቀናጀት የተከናወነም ነው።
እነዚህ ሥራዎች የከተማ እና ተፈጥሯዊ መዳረሻዎችን ወደ ሳቢ የቱሪዝም ማዕከልነት የለወጡ መኾናቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
Previous article“ዓለም የሚቀናባት፣ ኢትዮጵያ የምትደምቅባት”
Next article”ባሕር ዳር ሁልጊዜ ጽዱ እንድትኾን እንሠራለን” ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው