
አዲስ አበባ፡ ጥር 08/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በሕንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር አኒል ኩማር ራይ እና በኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመካከለኛው ምሥራቅ የፓስፊክ እና ኤዥያ ሀገራት ዳይሬክተር አምባሳደር ዳወን ከድር የዲፕሎማቶክ ቪዛ አገግልሎት ተፈራርመዋል።
የቪዛ አግልግሎት ስምምነቱ የአንዳቸው ሀገር ዲፕሎማት የዲፕሎማቲክ ፓስፖርት በመያዝ ቪዛ ሳያስፈልገው በሌኛው ሀገር መንቀሳቀስ የሚያስችል ነው።
ሕንድ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1948 በኢትዮጵያ ኢምባሲዋን ከከፈተች ወዲህ ትልቁ ዲፕሎማሲያዊ ስምምነት መሆኑን የተናገሩት በኢትዮጵያ የሕንድ አምባሳደር አኒል ኩማር ራይ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ወደ ስትራቴጂካዊ ትብብር ማደጉን ተናግረዋል።
በኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመካከለኛው ምሥራቅ የፓስፊክ እና ኤዥያ ሀገራት ዳይሬከተር አምባሳደር ዳወን ከድር ይህ ስምምነት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) እና የሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የተፈራረሟቸው ስምምነቶች ውጤት መሆኑን ገልጸዋል።
ሕንድ ኢትዮጵያ የኮፕ 32 አዘጋጅ መሆኗ ምን ያህል የዓለምን ትኩረት እንደሳበች ማሳያ መሆኑን በመጥቀስ የእንኳን ደስ ያለሽ መልእክት አስተልፋለችም ብለዋል አምባሳደሩ።
ኢትዮጵያ በበኩሏ የ2026 የብሪክስ ሊቀመንበር የሆነችው ሕንድ ዓለም አቀፍ የሰው ሠራሽ አስተውሎት 2026 ጉባኤ አስተናጋጅ በመሆኗ የእንኳን ደስ ያለሽ መልእክቷን በስምምነቱ ወቅት ገልጻለች።
ዘጋቢ፦ አንዱዓለም መናን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
