
ባሕር ዳር: ጥር 07/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ በአማራ ክልል ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ሁመራ ከተማ ገብተዋል።
አምባሳደሩ ሁመራ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አሸተ ደምለውን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
አምባሳደሩ በሁመራ በሚኖራቸው ቆይታ ከሁመራ ከተማ ነዋሪዎች ጋር እንደሚወያዩ ተገልጿል። ከወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው የጤና ተቋማትን አገልግሎት አሰጣጥ ይጎበኛሉም ተብሏል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
