ሴቶች ከአባልነት ባለፈ በውሳኔ ሰጭነት አቅም ስፍራን እንዲይዙ እየተሠራ ነው።

6
አዲስ አበባ: ጥር 04/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ምክር ቤት መደበኛ ሥብሠባውን እያካሄደ ነው።
ሥብሠባው የክንፉን የስድስት ወር አፈፃፀም መገምገም፣ ምርጫ እና የሴቶች ተሳትፎ ላይ ውይይት ማካሄድ እና የሴቶች ክንፍ መደበኛ ጉባኤ ላይ ትኩረት አድርጓል።
የፓርቲው የሴቶች ክንፍ ፕሬዝዳንት ዛህራ ሁመድ አባላትን ማብዛት እና እጩዎችን የመመልመል ሥራ ይሠራልም ብለዋል።
ሴቶች ከአባልነት ባለፈ የኢትዮጵያን ብልጽግና ማረጋገጥ የሚያስችል ብቃት ያላቸው አንዲኾኑ እና በውሳኔ ሰጭነት አቅም ስፍራን እንዲይዙ እየተሠራ እንደኾነም አስገንዝበዋል።
የክንፉ ምክትል ፕሬዝዳንት መስከረም አበበ ፓርቲው በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በክልል ምክርቤቶች እና በፌዴራሉ ፓርላማ የሴቶች ተሳትፎ መጠን 42 እና 43 በመቶ መኾኑን ተናግረዋል።
ይህን መጠንም የተሻለ ለማድረግ እየተሠራ ነው ብለዋል። የፀናች እና የበለጸገች ኢትዮጵያ በሚል ከጥር 12/2018 ዓ.ም እስከ የካቲት 12/2018 ዓ.ም ድረስ ለአንድ ወር የሚቆይ 8 ሚሊዮን አባላት እና ደጋፊ ሴቶች ጋር የንቅናቄ መድረክ እንደሚያካሂድም ገልጸዋል።
በንቅናቄ መድረኩ ሴቶች በሀገረ መንግሥት ግንባታ ያላቸው ሚና፣ በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካ እና በማኅበራዊ ተሳትፎአቸውን መገምገም እና ማሳደግ የሚያስችሉ ውይይቶች ይካሄዳሉ ነው ያሉት።
ዘጋቢ፦አንዱዓለም መናን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleተማሪዎች ውጤታማ እንዲኾኑ ምን እየተሠራ ነው?
Next articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የኢምግሬሽን እና ዜጎች ጉዳይ አገልግሎትን ጎበኙ።