
ባሕር ዳር፡ ጥር 03/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባስተላለፉት መልእክት “ዛሬ ጠዋት ጂቡቲ ስደርስ ክቡር ፕሬዝደንት ኢስማኤል ኦማር ጉሌህ አቀባበል አድርገውልኛል” ብለዋል።
ውይይታችን በጆኦፖለቲካል ጉዳዮች፣ በቀጣናዊ ሰላም እና ፀጥታ ብሎም የሁለትዮሽ ትብብራችንን በተለይም በንግድ፣ ሎጂስቲክስ እና የልማት ሥራዎች በምናጠናክርበት ኹኔታ ላይ ያተኮረ ነበር ሲሉም ገልጸዋል። ይኽም ለሰላም እና መረጋጋት፣ የኢኮኖሚ ትስስር እና የጋራ ብልጽግና ያለንን የወል ጽኑ አቋም የሚያመለክት ነው ብለዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
