“ኢትዮጵያ እና ቻይና ለአስርት ዓመታት የዘለቀ ጠንካራ ግንኙነት አላቸው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)

21
ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 30/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ይን ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኀበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ኢትዮጵያ እና ቻይና ለአስርት ዓመታት የዘለቀ ጠንካራ ግንኙነት አላቸው። ይኽ ግንኙነት በቅርቡ ወደ በሁኔታዎች የማይለዋወጥ የስትራቴጂክ ትብብር አድጓል ብለዋል።
ዛሬ የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ይን ተቀብዬ በጽናት በሚጓዘው የኢትዮጵያ እና ቻይና የመንግሥት እና ሕዝብ ግንኙነት ላይ ተነጋግረናል ነው ያሉት። በተለያዩ የልማት ትብብር ርዕሰ ጉዳዮችን ለማከናወን ያለንን ጽኑ አቋም በማስቀጠል ላይ ውይይት አድርገናል ብለዋል።
በኢኮኖሚ፣ ንግድ፣ መሠረተ ልማት፣ የኃይል አቅርቦት ፣ ትራንስፖርት፣ አዲስ በመፈጠር ላይ ባሉ እንደ ኢ-ኮሜርስ፣ ዲጂታል ኢኮኖሚ፣ ሰው ሰራሽ አስተውሎት እና አረንጓዴ ኃይል ልማት ላይ ትብብራችንን ለማጠናከር ተወያይተናል ነው ያሉት በመልዕክታቸው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየፈተና ውጤት ማሳወቅ
Next articleየገታራ በራራ በሽሎ ወንዝ አሞር ገደል መሻገሪያ ተንጠልጣይ ድልድይ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ክፍት ኾነ።