
ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 29/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በተለያዩ ሀገራት በተለይም በኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት ተከብሮ መዋሉን አልጄዚራ ዘግቧል።
የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ኢትዮጵያን ጨምሮ በመካከለኛው ምሥራቅ እስያ እና በምሥራቅ አውሮፓ ሀገራት በድምቀት የሚከበር ሲኾን ሩሲያ፣ ዩክሬን፣ ኢትዮጵያ፣ ግብጽ፣ ጆርጂያ፣ ቤላሩስ፣ ሰርቢያ፣ ካዛኪስታን፣ ሞልዶቫ፣ ኤርትራ፣ ሰሜን መቄዶንያ እና ሞንቴነግሮ በዓሉን አክብረው ውለዋል።
በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ልዩ ሥፍራ የሚሰጠው የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በዋዜማው እኩለ ሌሊት ላይ የበዓሉ ሥነ ሥርዓት በሁሉም አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ይቀርባል።
በአገልግሎቱ መጨረሻ ላይ የቤተልሔምን ኮከብ የሚወክል ሻማ ቀርቦም ይለኮሳል።
በኦርቶዶክስ ቀኖናዎች መሠረት አማኞች ኢየሱስ ክርስቶስን የሚያወድሱ ዝማሬዎችንም ይቀርባሉ።
ይህ ሁነት በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናትን ሁሉንም አንድ ያደርጋቸዋል።
በኢትዮጵያ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞች ዘንድ በኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል የፍስክ ምግብ የተለመደውን ያህል በሌሎች ዓለማት የሃይማኖቱ ተከታዮች ዘንድም የተለያዩ የበዓል ምግቦች ይቀርባሉ።
በሩሲያ ውስጥ “ኩቲያ” የሚባል ከስንዴ እና ከሩዝ የተሠራ ልዩ ገንፎ በገና ዋዜማ ይዘጋጃል።
ብዙውን ጊዜ አንድነትን በሚያመለክት የጋራ ጎድጓዳ ሳህን ላይ በማድረግ በጋራ ይመገባሉ።
አንዳንድ ቦታዎችም ምግብን እስከ ጣሪያው ድረስ የመወርወር ባሕል እንዳላቸው ይነገራል።
ከጣሪያው ጋር ከተጣበቀ መልካም ዕድል እንደሚያመጣ ይታመናል።
በአንድም ኾነ በሌላ ቅርጽ እና ይዘቱ ቢለያይም የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በመንፈሳዊ እና በባሕላዊ ሁነቶች በዓለም ዙሪያ በድምቀት ተከብሯል።
በደመወዝ የቆዬ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
