
ባሕር ዳር: ታሕሣሥ 29/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በገና ዋዜማ በመስቀል ዐደባባይ የቀረበው የአእላፋት ዝማሬ መንፈሳዊ ትዕይንት አስደናቂ እንደነበር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወጣቶች ጨዋነት እና ሥነ ሥርዓት በሞላበት መንገድ ሃይማኖታቸውን መግለጣቸው ስለ መጪው ትውልድ ያለንን አመለካከት የሚቀይር ነው ብለዋል በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት።
ትውልዱ ዕድሉ ከተሰጠው ከአስፈሪና አስጊ ነገሮች ርቆ መልካም የሆነውን መንገድ እንደሚከተል አሳይተዋል ነው ያሉት።
የሃይማኖት እንቅስቃሴዎች የራስን በመግለጥ፣ ሌላውን በማክበርና የጋራ ዕሴት በመፍጠር ላይ ከተመሠረቱ ለሀገር የሚያስገኙት ዋጋ ከፍ ያለ መኾኑንም አስረድተዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
