
ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 75ኛ ዓመት የምሥረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ “የምሁራን ሚና ለሀገራዊ ብልጽግና” በሚል ርዕስ የጥናታዊ ጽሁፍ አቅርበዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኀበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት “ምሁር ማነው?” ፣ ምሁር በስሜታዊነት የሚነዳ ሰው አይደለም ብለዋል።
የምሁር መገለጫዎች ሲያብራሩም ምሁር ሐሳብ አክባሪ እና አፍቃሪ፣ ጥልቅ አሰላሳይ እና ብዙ ጠያቂ፣ እንባቢ፣ ነቃሽና ተንታኝ፣ ችግር ፈቺና መፍትሔ አሳሽ መኾኑን ገልጸዋል።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 75ኛ ዓመት ክብረ በዓል ላይ የነበራቸው አቅርቦት በእነዚህ ጭብጦች ላይ ያተኮረ መኾኑን ገልጸዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
