
ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 22/2018 ዓ.ም አሚኮ) የአገው ፈረሰኞች ባዓልን በዩኔስኮ የሰው ልጆች ወካይ ቅርስነት ለማስመዝገብ ከባለድርሻ አካላት ጋር የጥናት ወርክሾፕ በባሕር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው።
በመድረኩ በምክትል ርእሰ መሥተዳደር ማዕረግ የከተማ እና መሠረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪ እና የርእሰ መሥተዳደሩ ተወካይ አሕመዲን ሙሐመድ (ዶ.ር)፣ በምክትል ርእሰ መሥተዳደር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር)፣ የፌዴራል ቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው፣ የአማራ ክልል ባሕል ቱሪዝም እና ስፖርት ቢሮ ኀላፊ መልካሙ ፀጋየ፣ የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ዋና አሥተዳዳሪ ቴዎድሮስ እንዳለውን ጨምሮ ሌሎች የፌዴራል፣ የክልል እና የዞን መሪዎች፣ የአገው ፈረሰኞች በዓል አስተባባሪዎች እና አባላት እንዲሁም ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።
የክልሉ የባሕል ቱሪዝም እና ስፖርት ቢሮ ኀላፊ መልካሙ ፀጋየ ከ1933 ዓ.ም ጀምሮ ማክበር የተጀመረው የአገው ፈረሰኞች በዓል 86ኛ ዓመቱን ጥር 23/2018 ዓ.ም ያከብራል ብለዋል።
ይሄን ውብ፣ ሳቢ እና ማራኪ የኾነ የአገው ፈረሰኞች በዓል ከሀገር አልፎ በዓለም ቅርስነት እንዲመዘገብ ሰፊ ሥራ እየተሠራ መኾኑን ገልጸዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
