
አዲስ አበባ: ታኅሣሥ 09/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት ተወካይ እና የባንኩ የኮርፖሬት አገልግሎት ኤክስኪዩቲቭ ምክትል ፕሬዝዳንት ኤፍሬም መኩሪያ፤ የሀገሪቱ ትልቅ ዘርፍ በኾነው የግብርና ዘርፍ ላይ ባንኩ የብድር አገልግሎት በመሥጠት እየሠራ ይገኛል ብለዋል።
ባንኩ አሁንም አነስተኛ ይዞታ ያላቸው እና ተደራጅተው የሚሠሩ አርሶ አደሮችን በማሽን ግዥ እና በሌሎች የግብርና ዘርፎች ተደራጅተው እንዲሠሩ የሚያችል የብድር አገልግሎትን ይፋ ማድረጉን ገልጸዋል።
ይህ የብድር አገልግሎት የግብርና ኢኮኖሚ ለማሳደግ የሚያግዝ መሬት እያላቸው በፋይናንስ እጦት ችግር ውስጥ የገቡ አርሶ አደሮችን ማገዝ የሚያስችል ነው ተብሏል።
ይህ ብርድር አርሶ አደሮችን እና አርብቶ አደሮችን ተጠቃሚ የሚያደርግ መኾኑም ተገልጿል። የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ መለስ መኮንን (ዶ.ር) በበኩላቸው ፋይናንስ ለግብርና ዋነኛ መሠረት ነው በማለት ንግድ ባንክ በዘርፉ እየሠራው ያለው ሥራ የሚበረታታ ነው ብለዋል።
ምርትና ምርትነትን በማሳደግ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የግብርና ፋይናንስ ወሳኝ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው በዚህ ሂደት ውስጥ ባንኮች ሚና አላቸው ነው ያሉት።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
