
ከሚሴ: ታኅሣሥ 08/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በመድረኩ በምክትል ርእሰ መሥተዳደር ማዕረግ የገጠር ልማት ዘርፍ አሥተባባሪ ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር) በሀገር መከላከያ ሠራዊት የልዩ ዘመቻዎች እዝ ምክትል አዛዥ ሜጀር ጀነራል አበባው ሰይድ፣ የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ መካሻ ዓለማየሁን ጨምሮ ሌሎች የክልል እና የዞኑ ከፍተኛ መሪዎች ተሳትፈዋል።
የሸዋ ሮቢት ከተማ አሥተዳደር ነዋሪዎች ከዚህ ቀደም በሰላም መደፍረስ በርካታ ችግር ያጋጥማቸው እንደነበር ገልጸው አሁን ላይ በተሠራው ሥራ አንፃራዊ ሰላም መፈጠሩን ተናግረዋል።
ከአጎራባች አካባቢዎች ጋር አሁን ላይ ሰላም በመፍጠር በጋራ መሥራት መጀመራቸውንም ገልጸዋል። የሰሜን ሸዋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ኤልያስ አበበ የሸዋ ሮቢትን እና አካባቢውን ሰላም ዘላቂ ለማድረግ የሀገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት መሪዎች ከአካባቢው መዋቅር ጋር በመኾን ሊሠሩ ይገባል ብለዋል።
የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ መካሻ ዓለማየሁ ባለፉት ጊዜያት ከአጎራባች የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ጋር በጋራ በተሠራው የሰላም ተግባር በቀጣናው አስተማማኝ ሰላም መፍጠር እንደተቻለ አስረድተዋል።
የሸዋ ሮቢት ከተማ ያለ ዘር እና ሃይማኖት ልዩነት ሁሉም የሚኖርባት ”የብኀነት ከተማ ናት” ብለዋል። ማኅበረሰቡ በቀጣይም ተቻችሎ በጋራ የመኖር እሴቱን አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባልም ብለዋል።
በሀገር መከላከያ ሠራዊት የልዩ ዘመቻዎች እዝ ምክትል አዛዥ ሜጀር ጀነራል አበባው ሰይድ የሸዋሮቢትን እና አካባቢውን ሰላም ዘላቂ ለማድረግ ሕዝብ እና መንግሥት በትብብር ሊሠሩ እንደሚገባ አሳስበዋል።
የሸዋሮቢት ከተማ ሕዝብ በታጣቂ ቡድኑ ተደጋጋሚ ችግር የደረሰበት በመኾኑ እኩይ ተግባሩን የተረዳ ማኅበረሰብ ነው ብለዋል። በቀጣይም ይህን ቡድን ማኅበረሰቡ ከፀጥታ ኀይሉ ጋር በመኾን ሊታገል እንደሚገባም ተናግረዋል።
በምክትል ርእሰ መሥተዳደር ማዕረግ የገጠር ልማት ዘርፍ አሥተባባሪ ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር) ከተማ አሥተዳደሩ አሁን ላይ አንፃራዊ ሰላም በመፍጠር በከተማው እየተሠሩ ያሉ የልማት ሥራዎች አበረታች ናቸው ብለዋል።
መንግሥት አኹንም ለሰላም የከፈተው በር ክፍት መኾኑን ጠቅሰው የሃይማኖት መሪዎች እና የሀገር ሽማግሌዎች ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ አካላትን ወደ ሰላም እንዲመጡ ጥሪ እንዲያደርጉም አሳስበዋል።
በቀጣይ ማኅበረሰቡን የሰላሙ ባለቤት ለማድረግ እንደሚሠራም አሥረድተዋል።
ዘጋቢ:- ይማም ኢብራሒም
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
