
ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 8/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ እና ሕንድ ያላቸው የረጅም ጊዜ ታሪካዊ፣ ባሕላዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ትብብር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሕንዱ አቻቸው ናሬንድራ ሞዲ ኢትዮጵያን ዳግም እንደሚጎበኙ ያላቸውን ተስፋ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።
ይህ ጉብኝት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ዘላቂ የሁለትዮሽ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋግራል ተብሎ ይጠበቃል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
