ሰላም የሚያደፈርሱ አካላትን እናቶች ሊመክሩ ይገባል።

3
ደብረ ብርሃን: ታኅሣሥ 08/2018 ዓ.ም (አሚኮ) “የሴቶች ሚና ለዘላቂ ሰላምና ሁሉን አቀፍ ልማት” በሚል መሪ መልዕክት በሰሜን ሸዋ ዞን አንጎለላና ጠራ ወረዳ ሴቶችን ያሳተፈ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው።
በምክትል ርእሰ መሥተዳደር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር) ባስተላለፉት መልዕክት ሰላም እንዲጸና እንዲሁም ልማት እንዲረጋገጥ ሴቶች ጉልህ አበርክቶ አላቸው ብለዋል።
የሰላም እጦት ዘርፈ ብዙ ዋጋ ያስከፍላል ያሉት ዶክተር ሙሉነሽ በተለይም ሴቶች የችግሩ ቀዳሚ ተጎጂዎች እንደኾኑ ጠቅሰዋል።
አስገድዶ መደፈርን ጨምሮ ለስነ ልቦናዊ ጫና፣ ለጾታዊ ጥቃት እና ለምጣኔ ሀብታዊ ችግር ቀድመው የሚጋለጡት ሴቶች መኾናቸውን አንስተዋል።
ሰላም የሚያደፈርሱ አካላትን እናቶች ሊመክሩ እና ወደ ሰላም እንዲመጡ የሚያስችል ሥራ ሊሠሩ ይገባል ነው ያሉት።
እንደ ክልል የተጀመሩ ምጣኔ ሀብታዊ እና ማኅበራዊ የልማት ሥራዎችን በማጠናከር የሕዝቡን የተጠቃሚነት አድማስ ይበልጥ ለማስፋት ዘላቂ ሰላምን ማስፈን ያስፈልጋል ብለዋል።
በውይይቱ ላይ የክልል፣ የሰሜን ሸዋ ዞን የሥራ ኅላፊዎች እና ከወረዳው የተውጣጡ ሴቶች እየተሳተፉ ነው።
የሥራ ኀላፊዎቹ በአንጎለላና ጠራ ወረዳ የተከናወኑ ልዩ ልዩ የልማት ሥራዎችን ተመልክተዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
Previous articleበሁሉም አማራጮች እርስዎን ለማገልገል ሁሌም ዝግጁ ነን!
Next article“የኢትዮጵያ እና ሕንድ የረጅም ጊዜ ታሪካዊ ግንኙነት ተጠናክሮ ይቀጥላል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)