የግብርና ሚኒስቴር ተሽከርካሪዎችን ለክልሎች አስረከበ።

7
አዲስ አበባ: ታኅሣሥ 06/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ግብርና ሚኒስቴር 267 የመስክ ተሽከርካሪዎች፣ 1 ሺህ 854 ሞተር ሳይክሎች፣ 2 ሺ 289 ፓምፖች እና ሌሎች መገልገያዎችን ለ12 ክልሎች እና ለሁለቱ ከተማ አሥተዳደሮች በድጋፍ አስረክቧል።
በርክክቡ ወቅት ንግግር ያደረጉት የግብርና ሚኒስትሩ አዲሱ አረጋ መንግሥት የግብርና ትራንስፎርሜሽን ትልምን ለማሳካት ያልታረሰ መሬቶችን በማረስ፣ መስኖን በማስፋፋት፣ የሜካናይዜሽን ማሽኖችን ለአርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች ለማዳረስ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ ነው ብለዋል።
ተሽከርካሪዎቹ እና መገልገያ መሳሪያዎቹ ሀገሪቱ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ፣ የኤክስፖርት ምርቶችን ለማሳደግ፣ ገቢ ምርቶችን መተካት እና የኢንዱስትሪ ግብዓቶችን በብዛት እና በጥራት ለማምረት የያዘችውን እቅድ ለማሳካት እንደሚያግዝ የግብርና ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
ተሽከርካሪዎቹ እና መገልገያዎቹ በምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም (FSRP) እና የአየር ንብረት የሚቋቋም የስንዴ እሴት ሰንሰለት ልማት ፕሮጀክት (CREW) የተገዙ ነው ያሉት።
ተሽከርካሪዎቹ ከ2 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው ሲኾን የFSRP እና የCREW ፕሮጀክቶች በሚተገበርባቸው ወረዳዎች የግብርና ትራንስፎርሜሽን ለማሳካት አገልገሎት ላይ የሚውሉ መኾናቸው ተገልጿል።
ዘጋቢ: – ኢብራሂም ሙሃመድ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
Previous articleሰላምን መከተል መሸነፍ ሳይኾን ለሀገር እና ለወገን ያለን ክብር ማሳየት ነው።
Next article“የትምህርት መሠረቱ ቅድመ መደበኛ ትምህርት ነው” አቶ አሸተ ደምለው