ሰላምን ለማረጋገጥ መንግሥት ከሕዝብ ጋር ተቀራርቦ መወያየትን ባሕል አድርጎ እየሠራ ነው።

9
ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 04/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር “የጉባ ብስራቶች፣ የመደመር መንግሥት ትሩፋቶች” በሚል መልዕክት ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍል ተወካዮች ጋር ውይይት እያደረገ ነው።
በውይይቱ የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፉ፣ የገብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ፣ የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው እና ሌሎች ከፍተኛ መሪዎች ተገኝተዋል።
የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው የኢትዮጵያውያን ታሪክ እና ነጻነት በኢትዮጵያውያን የጋራ ውጤት የተመሠረተ መኾኑን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያውያን ታሪክ ጸንቶ የዘለቀውም ማኅበረሰቡ ባለው የእርስ በርስ ትስስር መኾኑን ተናግረዋል።
የሚያኮራ ባሕል ያለውን ያህል አብሮ የዘለቀ የግጭት እና የድህነት ታሪኮች መኖራቸውን ገልጸዋል። ችግሩ አሁንም መቀጠሉን ነው ያነሱት።
ላለፉት ዓመታት ፈተና ኾኖ የዘለቀውን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት መንግሥት እየተሠራ ይገኛል ብለዋል።
የክልሉ መንግሥት ከፌደራል መንግሥት እና ከማኅበረሰቡ ጋር በመቀናጀት በሠራው ሥራ የክልሉ የሰላም ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱን ገልጸዋል።
በክልሉ የታየው የሰላም መሻሻል ይበልጥ እንዲረጋገጥ እና የተጀመሩ የልማት ሥራዎች ፍጻሜ አግኝተው ለሕዝብ ክፍት እንዲኾኑ ማኅበረሰቡ የሰላም ዘብ እንዲኾን አሳስበዋል። የሰላም ችግሩን በመፍታት ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን እና አብሮነትን ማጠናከር እንደሚገባም ጠይቀዋል።
በውይይቱ ላይ የተገኙት የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ.ር) እንዳሉት ያደጉ ሀገራት የሕዝባቸውን ኑሮ ለማሻሻል ትኩረት ሰጥተው በሚሠሩበት ዓለም ኢትዮጵያ ወደ ኋላ እንድትቀር የውስጥ እና የውጭ ጠላቶች እየሠሩ ይገኛሉ ብለዋል። መንግሥት እነዚህን ችግሮች ከመፍታት ጎን ለጎን ትላልቅ የልማት ሥራዎችን እየሠራ መኾኑንም አንስተዋል።
የተጀመረውን ሰላም ይበልጥ ለማረጋገጥ ደግሞ መንግሥት ከሕዝብ ጋር ተቀራርቦ መመካከር እና መወያየትን ባሕል አድርጎ እየሠራ መኾኑን ገልጸዋል።
ሉዓላዊነት የሚከበረው በጦርነት ብቻ ሳይኾን በምግብ ራስን በመቻል በመኾኑ ማኅበረሰቡ የሰላም ዘብ እንዲኾን ጠይቀዋል።
ዘጋቢ፦ ዳግማዊ ተሠራ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየምዕራብ አርሲ ዞን እና የሻሸመኔ ነዋሪዎችን ያሳተፈ ሕዝባዊ ውይይት በሻሸመኔ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
Next articleየፖሊዮ በሽታን ለመከላከል እየተሠራ ባለው ተግባር ማኅበረሰቡ አጋዥ መኾን አለበት።