“የጉባ ብስራቶች፤ የመደመር መንግሥት ትሩፋት”በሚል መሪ ሃሳብ ሕዝባዊ ውይይት በሸገር ከተማ አስተዳደር ተጀምሯል።

11
በሸገር ከተማ አስተዳደር “የጉባ ብስራቶች፤ የመደመር መንግሥት ትሩፋት” በሚል መሪ ሃሳብ ከባለፈው ሣምንት የቀጠለ የሕዝብ ውይይት መካሄድ ጀምሯል።
በውይይቱ ላይ የኢንዱስትሪ ሚንስትር መላኩ አለበል፣ የሲዳማ ክልል ብልጽግና ፓርታ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አብርሃም ማርሻሎ፣ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አብዱላዚዝ ዳውድ (ዶ.ር)፣ የሸገር ከተማ ከፍተኛ አመራሮች እና በየደረጃው ያሉ የሥራ ኀላፊዎች፣ አባገዳዎች፣ ሃደ ሲንቄዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እንዲሁም ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች የመጡ የሸገር ከተማ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
እየተካሄደ በሚገኘው ሕዝባዊ ውይይት የሚወሰደውን ግብዓት መነሻ በማድረግ በመጪው ጊዜ መንግሥት በማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ መስኮች በቅደም ተከተል መተግበር የሚኖርባቸውን የከተማዋን ጥያቄዎች ለመመለስ የሚረዱ በርካት ግብዓቶች ይሰበሰባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
Previous article‎‎”የጉባ ብስራቶች፤ የመደመር መንግሥት ትሩፋቶች” ሕዝባዊ የውይይት መድረክ በአርባ ምንጭ እየተካሄደ ነው።
Next articleየምዕራብ አርሲ ዞን እና የሻሸመኔ ነዋሪዎችን ያሳተፈ ሕዝባዊ ውይይት በሻሸመኔ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡