
“የጉባ ብስራቶች፣ የመደመር መንግሥት ትሩፋቶች” በሚል መሪ መልዕክት ሕዝባዊ የውይይት መድረክ በአርባምንጭ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።
የውይይት መድረኩ የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ሽመልስ አብዲሳ እና የብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር ጄነራል ታዜር ገብረእግዚአብሔር በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል።
በውይይት መድረኩ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች፣ ምሁራን፣ የጋሞ አባቶች፣ የሃይማኖት መሪዎች እና ከሁሉም የኅብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ ተወካዮች እየተሳተፉ ነው።
