
ጎንደር: ታኅሣሥ 03/2018 ዓ.ም (አሚኮ) “በመደመር መንግሥት ዕይታ፤ የዘርፎች እምርታ” በሚል መሪ መልዕክት የማዕከላዊ ጎንደር ዞን እና የጎንደር ከተማ አሥተዳደር የ3ኛ ዙር የመካከለኛ እና የጀማሪ መሪዎች ሥልጠና ተጠናቅቋል።
በማጠቃለያ መርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አወቀ አስፈሬ ሥልጠናው በግብርና፣ በከተማ ልማት፣ በቱሪዝም እና በኢንዱስትሪ ልማት ላይ አተኩሮ ሲሰጥ መቆየቱን ተናግረዋል። ውጤታማ ተግባራትን ለመከወን የሚያስችል እንደነበርም አንስተዋል።
ኢኮኖሚውን ሊያሻግሩ የሚችሉ ሃሳቦችን መተግበር ፣ “ቅንጅታዊ አሠራርን ማጠናከር እና የአፈጻጸም ብቃትን ማሳደግ ከመሪዎች ይጠበቃል” ነው ያሉት።
መሪዎች በሥልጠና ያገኙትን ዕውቀት ወደ ተግባር መቀየር አለባቸውም ብለዋል። ይህንን ተግበራዊ ለማድረግም ሰላም ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ መኾኑን የገለጹት ዋና አሥተዳዳሪው አሁን የተገኘውን ሰላም ለማጽናት በቀጣይም የሚሠራ መኾኑን አንስተዋል።
የውይይቱ ተሳታፊዎች ሥልጣው ከዚህ በፊት ሲሰጡ ከነበሩ ሥልጠናዎች በተለየ መልኩ ተግባር ላይ ትኩረት ያደረገ እና ለውጥ ለማምጣት የሚያሰችል አቅም ያገኙበት መኾኑንም አረጋግጠዋል።
በሥልጠናው ያገኙትን አቅም ተጠቅመው ሴቶች እና ወጣቶችን ጨምሮ ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍሎች በግብርና፣ በቱሪዝም እና በሌሎችም ልማቶች ተጠቃሚ እንዲኾኑ ቅድሚያ ሰጥተው እንደሚሠሩም ነግረውናል ።
ዘጋቢ:- ቃልኪዳን ኃይሌ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
