
ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 03/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል መንግሥት እና በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) መካከል የተደረገውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ የታጠቁ ኃይሎች ወደ ሰላም እየገቡ ነው።
በምዕራብ በለሳ ወረዳ በተለያዩ አካባቢዎች ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 65 የፋኖ አባላት የሰላም ጥሪውን ተቀብለዋል።
የሰላም አማራጩን ለተቀበሉ የፋኖ አባላት የምዕራብ በለሳ ወረዳ ዋና አሥተዳዳሪ በላይነህ አዛናው፣ የዞን ደጋፊ የሥራ ኀላፊ የኾኑት ጀንበሩ ሞላ እና የ57ኛ ክፍለ ጦር 2ኛ ሬጅመንት ምክትል አዛዥ መቶ አለቃ ከፍያለው አያናው አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የሰላም ጥሪውን የተቀበሉ የፋኖ አባላት ዘላቂ ሰላም እና ልማት እንዲረጋገጥ ከመንግሥት ጋር ኾነን እንሠራለን ብለዋል።
ከዚህ በፊት በተለያየ መንገድ የበደልነውን ሕዝብ ለመካስ ተዘጋጅተናል ነው ያሉት።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
