የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት፦

13
ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 02/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በትብብር ሥራችን ኢትዮጵያን ከዓለም ንግድ በማስተሣሠር ወደ ላቀ ብልጽግና እናሸጋግራለን!
ዛሬ ሀገራችን ወደ ዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት የምታደርገውን ጉዞና የድርድር ሂደት አስመልክቶ በተዘጋጀው ታላቅ መድረክ ተገኝተናል።
ኢትዮጵያ የበርካታ ዓለም አቀፍ ተቋማት መሥራች ብትሆንም፣ ከዓለም የንግድ ድርጅትና የትሥሥር ሂደት ለረጅም ጊዜ ባይተዋር ሆና ቆይታለች።
የመደመር መንግሥት በወሰደው ጠንካራ አመራርና ቁርጠኝነት በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያዎቻችን ከሁለት ዐሠርት ዓመታት በላይ የዘለቀው የአባልነት የድርድር ጉዞ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ደርሷል። በተለይም ባለፉት ሰባት ወራት የተመዘገቡ ስኬቶች የድርድሩን መቋጫ የሚያሳዩ ናቸው።
የዓለም ንግድ ድርጅት አባል መሆናችን የገበያ ተደራሽነትን ያሰፋልናል፤ የንግድና ኢንቨስትመንት ግልጽነትና ተገማችነትን በማጎልበት ተመራጭነታችንን ያሳድጋል።
የድርድሩን ሂደት በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ መንግሥት በቁርጠኝነት ይሠራል። ሂደቱ ቅንጅትን የሚሻ በመሆኑ የግሉ ዘርፍ፣ አስፈጻሚ ተቋማት ሚናቸውን እንዲወጡ ዓለም አቀፍ አጋሮችም ድጋፍቸውን እንዲያጠናክሩ ጥሪዬን አቀርባለሁ።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleአምራች ኢንዱስትሪዎቹ በጥሩ የሥራ እንቅስቃሴ ውስጥ ናቸው።
Next articleለሕዝባችን ያመጣነው ለውጥ ባለመኖሩ ወደ ዘላቂ የሰላም ስምምነት መጥተናል” አፋህድ