የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት፦

23
ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 01/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የወላይታ ሕዝብ ጥንታዊ ስልጣኔ መገለጫ፣ የበለፀገ ታሪክ እና ከሕዝቡ ማንነት ጋር ስር የሰደደ ትስስር ያለው የወላይታ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል የሆነው “ጊፋታ” በዩኔስኮ (UNESCO) በይፋ በመመዝገቡ የተሰማኝን ልባዊ ደስታ ለመግለጽ እወዳለሁ።
ጊፋታ ከአሮጌው ወደ አዲሱ፣ ከጨለማ ወደ ብርሃን መሸጋገርን የሚያበስር፤ እንዲሁም እርቅ እና ፍቅር የሚሰበክበት ታላቅ እሴት ነው።
“ጊፋታ” በዓለም ቅርስነት መመዝገቡ ለሀገራችን የቱሪዝም ዕድገት ተጨማሪ አቅም ከመፍጠሩም በላይ ድሉ ለመላው የወላይታ ሕዝብ እና ለኢትዮጵያውያን በሙሉ ትልቅ ኩራት ነው::
በድጋሜ እንኳን ደስ አለን!
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleማኅበረሰቡ ለሰላም አጋርነቱን ሊያሳይ ይገባል።
Next article“ለጋራ ሰላም በጋራ መቆም ይገባል” አማኑኤል ፈረደ (ዶ.ር)