
ደሴ: ኅዳር 29/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች የተመራ ልዑክ በደቡብ ወሎ ዞን ለጋምቦ ወረዳ በወቅታዊ ክልላዊ እና ሀገራዊ የሰላም እና የልማት ጉዳዬች ላይ ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር እየመከሩ ነው።
ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎቹ በአካባቢው ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። በውይይት መድረኩ ከደቡብ ወሎ ዞን ለጋምቦ ወረዳ፣ ከፊጣ ክላስተር የተውጣጡ ልዩ ልዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
በመድረኩ በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይርጋ ሲሳይ፣ በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኀላፊ ፍሰሐ ደሳለኝ፣ የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አሊ መኮንን እና ሌሎችም ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
ዘጋቢ:- ጀማል ይማም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
