
ባሕር ዳር: ኅዳር 29/2018 ዓ.ም (አሚኮ) 20ኛው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች በዓል በሆሳዕና ከተማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በተገኙበት እየተከበረ ነው፡፡
በዓሉ “ዴሞክራሲያዊ መግባባት፤ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ መልዕክት እየተከበረ ነው፡፡
በበዓሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)፣ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር፣ የፌደራል ጠቅላይ ፍድር ቤት ፕሬዚዳንት ቴዎድሮስ ምህረት፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ የክልል ርእሳነ መስተዳድሮች፣ አፈ ጉባኤዎች፣ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
20ኛው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች በዓል በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሆሳዕና ከተማ እየተከበረ ነው፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
