
አዲስ አበባ: ኅዳር 28/2018 ዓ.ም (አሚኮ) 20ኛውን የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን ምክንያት በማድረግ ውቧ ሆሳዕና ከተማ የምክክር ቀን መርሐ ግብርን እያካሄደች ትገኛለች።
ከደቂቃዎች በኋላ በሚጀምረው ሀገራዊ የሲምፖዚየም መድረክ ላይ ለመታደም የፌዴሬሽን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር፣ የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርእሰ መሥተዳድር እንደሻው ጣሰው (ዶ.ር)፣ የክልል ርእሳነ መሥተዳድሮች፣ የክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤዎች፣ የብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ተወካዮች ተገኝተዋል።
ሲምፖዚየሙ ዴሞክራሲ እና የፌዴራል ሥርዓት አተገባበር በኢትዮጵያ፣ የኢትዮጵያ የምርጫ ሥርዓት፣ የብዝኅነት አሥተዳደር በኢትዮጵያ እንዲሁም የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሕዝቦች የጋራ እሴቶች እና ጸጋዎች በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ምክክር እንደሚደረግ ይጠበቃል።
ዘጋቢ፦ ኢብራሒም ሙሐመድ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
