
ባሕር ዳር: ኅዳር 26/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ባልደረባ ጋዜጠኛ አበሻ አንለይ የራሽያ ቴሌቪዥን (RT) ባዘጋጀው የአፍሪካ ሚዲያ አዋርድ ላይ በአውት ስታንድንግ ዶክሜንታሪ (Outstanding Documentary) ዘርፍ የመጨረሻዎቹ ሦስት እጩዎች ውስጥ ተካቷል።
በነጻነት ተምሳሌቷ ኢትዮጵያ በተዘጋጀው አፍሪካ ሚዲያ አዋርድ ዝግጅት ከ800 በላይ ሥራዎች ለውድድር ቀርበዋል።
የአፍሪካ ሚዲያ ሽልማት የአፍሪካን የሚዲያ ገጽታ የሚቀርጹ ምርጥ ድምጾችን በማሰባሰብ ጋዜጠኝነትን፣ ብሮድካስትን፣ ዲጂታል ሚዲያን እውቅና የሚሰጥ ሽልማት ነው።
ከአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን የተዘጋጀው ምርጥ ዶክመንታሪ ከሦስት እጭዎች ውስጥ ተካቷል። በዝግጅቱ የሀገራት መሪዎች፣ የአሚኮን ጨምሮ ሌሎች የሚዲያ ሥራ አሥፈጻሚዎች በተገኙበት ለአሸናፊዎች እውቅና እና ሽልማት ፕሮግራም ተካሂዷል።
አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን አሚኮ በአህጉራዊ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ትስስር እና አንድነትን የሚፈጥሩ ዘገባዎችን በመሥራት ሚናውን እየተወጣ ያለ ተቋም ነው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
