የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት፦

10
ባሕር ዳር: ኅዳር 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የስታትስቲክስ መረጃ የምንመኘውን የአህጉራችን አፍሪካ ዕድገት ዕውን ለማድረግ የምንመራበት የልማት ካርታችን ነው።
ዛሬ የአፍሪካን የልማት አጀንዳ የሚመራውን የአፍሪካ ብሔራዊ ስታቲስቲክስ ዋና ዳይሬክተሮች ኮሚቴ 19ኛ መደበኛ ስብሰባ በአዲስ አበባ አስጀምረናል።
ኢትዮጵያ ለአስር ዓመት የልማት ዕቅድ እና ለሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ስኬታማነት ስታትስቲክስን በወሳኝ አቅምነት በመለየት ትኩረት ሰጥታለች። የስታትስቲክስ አገልግሎት ተቋሟንም እያዘመነች ትገኛለች።
ፖለሲዎቻችን፣ የልማት ትግበራዎቻችንና ውሳኔዎቻችንን ጥራት ባላቸው መረጃዎች ላይ የተመሰረቱ እንዲሆኑ እየሰራን እንገኛለን። የበለፀገችና ጠንካራ አፍሪካን የመፍጠር መሻታችንን በማሳካት ረገድም ስታትስቲክስ ወሳኝ ሚና አለው።
ስታቲስቲክስ የልማት ካርታችን ነው፤ የት እንዳለን ይነግረናል፣ ወዴት እንደምንሄድም ያሳየናል።
በመሆኑም በአፍሪካ የስታትስቲክስ ተቋማዊ ነጻነትን ማጠናከር፣ ለስታትስቲክስ ዘላቂ ፋይናንስን ማረጋገጥ እና በአህጉሪቱ ወጥነት ያለው የመረጃ ሥርዓት መፍጠር ላይ ትኩረት መስጠት ይኖርብናል በማለት በማኅበራዊ ተስስር ገጻቸው አስፍረዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ከአልሚ ባለሃብቶች ጋር በባሕር ዳር ከተማ እየተወያዩ ነው።
Next articleየሃይማኖት አባቶች የሰላም መልዕክተኞች በመኾናቸው ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ በትኩረት ሊሠሩ ይገባል።