
ባሕር ዳር: ኅዳር 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በባሕር ዳር ከተማ ውስጥ ለልዩ ልዩ የሆቴልና ቱሪዝም አገልግሎቶች ቦታ ከወሰዱ ባለሃብቶች ጋር እየተወያዩ ነው።
በውይይቱ ላይ ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ፣ የአማራ ክልል ከተማ እና መሰረተ ልማት ቢሮ ኀላፊ ሞላ መልካሙ (ዶ.ር) የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው እና ሌሎችም የከተማ አሥተዳደሩ መሪዎች እየተሳተፉ ነው።
በባሕር ዳር ከተማ ባለኮከብ ሆቴሎችን በመገንባት የከተማዋን የቱሪዝም አቅም ከፍ እንደሚያደርጉ ታምኖባቸው ቦታ የወሰዱ 43 ባለሃብቶች እና ተወካዮቻቸውም ተገኝተዋል።
ባለሃብቶች መሬት ከወሰዱ በኋላ ሕንጻ ቢገነቡም አገልግሎት ግን መስጠት ያልጀመሩ፣ ሕንጻ ግንባታ ጀምረው ያላጠናቀቁ እና ቦታውን አጥረው ያስቀመጡ ናቸው።
የዛሬው ውይይት ዓላማም የባለሃብቶችን የልማት ተግዳሮቶች በጋራ በመፍታት በሙሉ አቅም ወደ ሥራ ለማስገባት ስለመኾኑ በውይይቱ መግቢያ ላይ ተገልጿል።
ዘጋቢ፦ አሚናዳብ አራጋው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
