
አዲስ አበባ: ኅዳር 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር የከተማውን ሥራ ፈላጊዎች ወደ ሥራ ለማስገባት የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ መኾኑን አስታውቋል።
በበጀት ዓመቱ በአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከ366 ሺህ በላይ ሥራ ፈላጊዎችን ወደ ሥራ ለማስገባት መታቀዱም ተገልጿል።
የዚህ አካል የኾነ እና ከተለያዩ ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ እና ሥልጠና ወስደው ያጠናቀቁ 30 ሺህ ሥራ ፈላጊዎችን በአንድ ጀንበር ወደ ሥራ የማስገባት ሥነ ሥርዓት ከተማ አሥተዳደሩ አካሂዷል።
በሥነ ሥርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አበቤ የከተማዋን ሥራ ፈላጊዎች ወደ ሥራ ለማስገባት ትኩረት መሠጠቱን ተናግረዋል።
በከተማው ያሉ ፀጋዎችን በመለየት ማለትም በግንባታ ዘርፍ፣ በንግድ አገልግሎት፣ በከተማ ግብርና እና በሌሎች ዘርፎች ሥራ ፈላጊዎች ሥልጠና ወስደው ወደ ተግባር ገብተዋል ብለዋል።
በከተማ አሥተዳደሩ የከተማውን ሥራ ፈላጊዎች ወደ ሥራ ለማስገባት የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ መኾኑን የተናገሩት ደግሞ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የሥራ እና ሥልጠና ቢሮ ኀላፊው ሚሊዮን ማቲዮስ ናቸው።
ዘጋቢ:- ተመስገን ዳረጎት
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
