አዲስ አበባ: ኅዳር 22/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ኦቪድ ሪል ስቴት በልዩነት ታላቅ የሽያጭ ኤክስፖ በአዲስ አበባ ከተማ ማዘጋጀቱን አስታውቋል።
ራዕያችን ልማት ነው የሚል መርሕ ያነገበው ኦቢድ ሪል ስቴት የተቋቋመው 2013 ዓ.ም ነበር። አዳዲስ የግንባታ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ደረጃቸውን የጠበቁ ቤቶችን በጥራት እና በፍጥነት እየገነባ በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ የመኖሪያ ቤት ችግርን ለማቃለል ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን እያከናወነ ነው።
በዚህም ብዙዎችን ተጠቃሚ አድርጓል።
የሪል ስቴት ዘርፉ ዋነኛ ማነቆ የኾነውን የአቅርቦት ሰንሰለት ችግር ለመቅረፍ የሚያስችል የተቀናጀ አሠራር ቀይሶ ወደ ሥራ የገባው ኦቪድ ሪል ስቴት በርካታ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት በማጠናቀቅ እና ቀድሞ በማስረከብ የመኖሪያ ቤትን ችግር እየቀረፈ ነው።
ኩባንያው ባለፉት ዓመታት ተግባራዊ ባደረጋቸው ፕሮጀክቶች በሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶችን ገንብቶ አጠናቋል። ከእነዚህ መካከል በአቧሬ መልሶ ማልማት ፕሮጀክት በ100 ቀናት ገንብቶ ያስረከባቸው የመኖሪያ እና የንግድ አገልግሎት የሚሰጡ ባለ ጂ ፕላስ 12 ዘመናዊ ሕንጻዎች ይጠቀሳሉ።
በዘመናዊ የግንባታ ቴክኖሎጂዎች እና በተሳለጠ የአቅርቦት ሰንሰለት ታግዞ ቤቶችን በጥራት እና በፍጥነት እየገነባ በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረብ መቻሉ ብዙዎችን የቤት ባለቤት ከማድረግ ባለፈ በየዓመቱ ከ25 እስከ 30 በመቶ የዋጋ ጭማሪ ይታይበት የነበረውን የሀገሪቱን የቤቶች ገበያ ዋጋ በማረጋጋት ከፍተኛ ቅናሽ እንዲፈጠር አድርጓል።
በርካታ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን በማከናወን ላይ የሚገኝም ነው። ከእነዚህ መካከል ግዙፉ የኦቪድ ገላን ጉራ ከተማ ፕሮጀክት በ750 ሄክታር ስፋት ባለው ቦታ ላይ በግንባታ የሚገኘው የግዙፍ ከተማ ፕሮጀክት ከ60 ሺህ በላይ መኖሪያ ቤቶችን የማኅበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማትን የንግድ እና የመዝናኛ ማዕከላትን ያሟላ ነው።
ኩባንያው በተጨማሪ በአዲስ አበባ ጥይት ቤት 1 እና 2 ጉለሌ፣ ቦሌ ጃፓን፣ ቦሌ መድኃኒዓለም እና ጫካ ፕሮጀክቶችን እየሠራም ይገኛል። በጅማ ከተማም የጀመረው የመኖሪያ ቤቶች ፕሮጀክት በተፋጠነ ግንባታ ላይ ነው ተብሏል።
ኦቪድ ሪል ስቴትን ጨምሮ በስሩ በሚገኙ በርካታ ኩባንያዎች ከ10 ሺህ በላይ ለሚኾኑ ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል የፈጠረ ግዙፍ ኩባንያ እና ታማኝ ግብር ከፋይ በመኾኑ በተደጋጋሚ ለሽልማት በቅቷል።
ኩባንያው ማኅበራዊ ኀላፊነቱን ከመወጣት አንጻር የአዋሬ መልሶ ማልማት ፕሮጀክት ጨምሮ በድምሩ ከ1 ሺህ 200 በላይ ቤቶችን ገንብቶ በነጻ ለተጠቃሚ አስተላልፏል።
ኦቪድ ሪል ስቴት በመኖሪያ ቤት እና በንግድ ሱቆች የመሸጫ ዋጋ ላይ ለረዥም ጊዜያት የቆየ ቅናሽ አድርጎ ከመጭው ታኅሣሥ 7 ጀምሮ ማስተካከያ ለማድረግ አቅዷል።
ደምበኞቹ የመጨረሻውን ቅናሽ ዕድል እንዲጠቀሙ ከኅዳር 22 እስከ ታኅሣሥ 6/2018 ዓ.ም ድረስ ብቻ የሚቆይ በአዲስ አበባ ከተማ በአምስት የተለያዩ ቦታዎች የሚካሄድ ልዩ ሽያጭ ኤክስፖን አዘጋጅቷል።
ኤክስፖው የመኖሪያ እና የንግድ ሱቆች በቅናሽ ለሽያጭ አቅርቦ ዓመች የክፍያ ሥርዓቶችንም አዘጋጅቷል።
ኤክስፖው የሚካሄድባቸው ቦታዎች ገርጂ፣ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ግቢ፣ ኦቪድ ገላን ጉራ ሳይት፣ አራት ኪሎ፣ ጥይት ቤት ሳይት፣ ኢትዮ ኩባ የወዳጅነት አደባባይ እና ጎልፍ ክለብ ግቢ ናቸው።
ሁሉም ፕሮጀክቶች ግንባታዎቹን በጥራት እና በፍጥነት በማጠናቀቅም ደንበኞቹን የቤት ባለቤት ለማድረግ በትጋት እንደሚሠራ ያረጋገጠው ኦቪድ ሪል ስቴት ኤክስፖውን በይፋ ክፍት አድርጓል።
ዘጋቢ:- አፈወርቅ አበዶም
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
