አስር የተተከሉ ከሳተላይት ያለማቋረጥ ዳታ የሚቀበሉ ጣቢያዎች ወይም CORS ሥራ ጀመሩ።

15
አዲስ አበባ: ኅዳር 22/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በቋሚነት መሬት ላይ የሚተከል የሳተላይት ዳታን ያለማቋረጥ የሚቀበል እና ፕሮሰስ የሚያደርግ መኾኑ ተገልጿል።
ቴክኖሎጂው የአንድን ቦታ መገኛ መረጃን ከጂፒኤስ ሳተላይቶች 24 ሰዓት ሙሉ በመቀበል ከፍተኛ ጥራት የሚሰጥ ነው።
በማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓቱ ተገኝተው ንግግር ያድጉት የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ኤዴታ ፈንታ ደጀን ቴክኖሎጂው ቀያሾች፣ ተመራማሪዎች፣ የአደጋ ተንታኞች፣ የመልክዓ ምድር እና የልዩ አገልግሎት ካርታ የሚያዘጋጁ ሙያተኞች መገኛን በሳንቲ ሜትር ደረጃ መረጃ የሚያገኙበት መኾኑን ገልጸዋል።
ከዚህ ቀደም የቅየሳ ሥራ ለመሥራት መነሻ የሚኾን የጂፒኤስ መሳሪያዎች መትከል የግድ የነበረውን አሠራር ያስቀረ ቴክኖሎጂ ነው ብለዋል፡፡
ተጠቃሚዎች ከዚህ በፊት ለመነሻ የሚኾን መረጃ ለመውሰድ ወደ ማዕከል ይመጡ የነበረውን በማስቀረት ባሉበት ቦታ ኾነው አገልግሎቱን በማስገኘት ጊዜን እና ተጨማሪ ወጪን ያድናል ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሙሉቀን ቀሬ የዲጂታል ኢትዮጵያን 2025 እውን ለማድረግ በርካታ ተግባራት እየተከናዎኑ ይገኛሉ ብለዋል።
የተተከሉ ከሳተላይት ያለማቋረጥ ዳታ የሚቀበሉ ጣቢያዎች ወይም CORS ለሀገሪቱ ዲጂታላይዜሽን ሥራዎች ስኬት የላቀ ሚና አላቸው ብለዋል።
የኢትዮጵያ የስፔስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር አብዲሳ ይልማ (ዶ.ር) እንደገለጹት ይህ ቴክኖሎጂ ለሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ዘርፎች ጥራት ያለው መረጃ በመስጠት እና በማዘመን ለስኬቱ ቁልፍ ድርሻ እንዳለው ተናግረዋል።
ለስማርት ሲቲ፣ ለታላቁ ኅዳሴ ግድብ፣ ለገበታ ለሀገር፣ ለአዲሱ ኤርፖርት ግንባታ ፈጣን መረጃ በመስጠት ትክክለኛ ውሳኔን ለመወሰን የሚያስችል ነውም ብለዋል።
በቀጣይም ተጨማሪ 10 ቴክኖሎጂዎችን ወደ ሥራ ለማስገባት በሂደት ላይ ሲኾን በሁለት ዓመታት ውስጥ ቴክኖሎጂውን ወደ 34 ለማድረስ ታቅዶ ወደ ሥራ መገባቱ ተገልጿል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
ዘጋቢ:- ኢብራሂም ሙሃመድ
Previous article“ጉዳዩን የተገነዘበ እና የተደራጀ ሕዝብ ሲኖር ሰላም አስተማማኝ ይኾናል” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ
Next articleኤች አይ ቪ ኤድስ ላይ ያለው መዘናጋት ዋጋ እያስከፈለ ነው።