በተባበሩት መንግሥታት የአየርንብረት ለውጥ ማሕቀፍ ኮንቬንሽን መሠረት የኢትዮጵያ የኮፕ 32 አስተናጋጅ ሀገር መሆኗን ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግሥት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑትን ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቴዎስን የኮፕ 32 ተወካይ ፕሬዝደንት አድርጎ መመደቡን ሲገልጽ ደስታ ይሰማዋል።

42
ዶክተር ጌዲዮን ከሀገር ውስጥ የሥራ ኃላፊዎች፣ ከተባበሩት መንግሥታት አካላት እና ዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር በመተባበር የኮፕ 32 ዝግጅትን የሚመሩ ይሆናል።
የኢትዮጵያ መንግሥት የተባበሩት መንግሥታት የአየርንብረት ለውጥ ማሕቀፍ ኮንቬንሽን አባል ሀገራት ለኢትዮጵያ የማዘጋጀት ኀላፊነት በመስጠታቸው ምስጋናውን እያቀረበ በዶክተር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ አስተባባሪነት ከዓለም የአየር ንብረት ጥበቃ ማኅበረሰብ ጋር በቅርበት ለመሥራት ዝግጁ መሆኑን ይገልፃል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት
Previous articleየኤች አይቪ ኤድስ ሥርጭትን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር መዘናጋቱ ሊቆም ይገባል።
Next articleከዐይን ሞራ ቀዶ ሕክምና በኋላ ለዕይታ በመብቃታቸው መደሰታቸውን ታካሚዎች ገለጹ።