
ባሕር ዳር: ኅዳር 15/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ለሲንጋፖር ጠቅላይ ሚኒስትር ላውረንስ ዎንግ በብሔራዊ ቤተ መንግሥት ይፋዊ የአቀባበል ሥነሥርዓት አካሂደዋል።
የአቀባበል ሥነ ሥርዓቱ ወዳጅነትን የሚያመላክት የዛፍ መትከል መርሐ ግብር፣ የብሔራዊ ሙዚየም ታሪካዊ ቅርሶች እና ምድረ ግቢ ጉብኝት፣ የሁለትዮሽ ውይይቶች በክህሎት ልማት እና የካርበን ብድር የመግባቢያ ስምምነቶች ፊርማን አስቀድሞ የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫን ያካተተ ነው።
የጠቅላይ ሚኒስትር ዋንግ ጉብኝት በሰኔ 2017 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በሲንጋፖር ያደረጉትን ጉብኝት ተከትሎ የተካሄደ ነው። በሁለቱ ሀገራት መካከል እያደገ የመጣውን ግንኙነት የሚያሳይም ነው ተብሏል።
ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ሁለቱም መሪዎች በጉብኝቱ የኢኮኖሚ ትብብርን ለማላቅ፣ ተቋማዊ መስተጋብርን ለማጠናክር እና የወል ቅድሚያዎቻቸውን ከፍ አድርጎ ለመከወን መንገዶችን ተመልክተውበታል ነው የተባለው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
