ሠራዊቱን በአካል እና በሥነ ልቦና በመገንባት በኩል በትኩረት እየተሠራ ነው።

18
ጎንደር: ኅዳር 15/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ በጎንደር ቀጣና ሲሰጥ የነበረው የሪፎርም እና የአቅም ግንባታ ሥልጠና ማጠቃለያ መርሐ ግብር ተካሂዷል።
የአቅም ግንባታ ሥልጠናው ለተከታታይ ስድስት ቀናት ሲሰጥ የቆየ ሲኾን ክልሉ ካጋጠመው የጸጥታ ችግር ለመውጣት የፖሊስ አባላት ኀላፊነታቸውን በተሻለ ሁኔታ መወጣት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተጨማሪ አቅም ለመፍጠር ያለመ ነው።
ከገጠመው የሰላም እጦት በመውጣት ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ሥራዎችን በበለጠ ተግባራዊ በማድረግ የሠራዊቱን አቅም ማጎልበት እንደሚገባ የተናገሩት የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ምክትል ኮሚሽነር እና የአሥተዳደር እና ልማት ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ረዳት ኮሚሽነር አያልነህ ተስፋዬ ናቸው።
በቀጣይ “ሠራዊቱን በአካል እና በሥነ ልቦና መገንባትን ጨምሮ ቅንጅታዊ ሥራዎችን በማጠናከር “ፈጣን የመረጃ ልውውጥ ሥርዓት መዘርጋት ላይ በትኩረት እንደሚሠራም ረዳት ኮሚሽነሩ አስገንዝበዋል።
ያለውን የሰው ሃብት የመፈጸም አቅም ለማሳደግ እና የተጀመረውን የአሠራር ስልት ለመተግበር የሃብት ብክነትን በማስወገድ እና የሃብት አሥተዳደር ሥርዓትን ማዘመን እና የቁጥጥር ሥርዓትን ማስፈን እንደሚገባም አስታውቀዋል።
ከሥልጠናው ተሳታፊዎች መካከል በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የምዕራብ ደምቢያ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር የጸዳው ምስጋናው ሥልጠናው ሰላምን በማስጠበቅ የሕዝብ አገልጋይነት መንፈስን የሚያጠናክር እና በቀጣይ ተገቢውን ሥራ ለመሥራት አቅም የሚፈጥር እንደነበር ተናግረዋል።
ሥልጠናው ፖሊስ ፍትሕን ለማስፈን በሚያከናውናቸው ተግባራት የበለጠ ውጤታማ እንዲኾኑ አቅም የሚፈጥር መኾኑንም አሳውቀዋል።
በሥልጠናው ልምድ መቅሰማቸውን ያነሱት የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ቃፍታ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ምክትል ኢንስፔክተር ትርሃስ አያሌው ሪፎርሙ የሴቶችን የመሪነት ሚና የሚያሳድግ እና ቀልጣፋ አሠራርን ለመተግበር የሚያግዝ መኾኑን አንስተዋል።
ዘጋቢ:- ማርታ አዱኛ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article“ከሲንጋፖር ጋር ይኽን የወዳጅነት እና የትብብር ጉዞ በጋራ በመቀጠላችን ክብር ይሰማናል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) 
Next articleየሲንጋፖር ጠቅላይ ሚኒስትር የኢትዮጵያ ጉብኝት በሁለቱ ሀገራት መካከል እያደገ የመጣውን ግንኙነት የሚያሳይ ነው።