“ከሲንጋፖር ጋር ይኽን የወዳጅነት እና የትብብር ጉዞ በጋራ በመቀጠላችን ክብር ይሰማናል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) 

17

ባሕር ዳር፡ ኅዳር 15/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የሲንጋፖር ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ላውረንስ ዎንግን ተቀብለው አነጋግረዋል።

 

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኀበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የሲንጋፖር ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ላውረንስ ዎንግን በክብር ተቀብያለው ብለዋል።

 

ውይይታችን በሁለቱ ሀገሮቻችን መካከል ያለንን ግንኙነት ለጋራ ነጋችን ወሳኝ በሆኑ መስኮች በጋራ ለመሥራት በምናደርገው ጥረት ውስጥ አንድ ጠቃሚ ርምጃ ነው። በተለይም በክሂሎት ልማት እና የካርበን ብድር ትብብር ላይ ያደረግናቸው የመግባቢያ ስምምነቶች ጽኑ እና ለነገው ገበያ ዝግጁ የሆኑ ሠራተኞችን ለማፍራት፣ በአየር ንብረት ጥበቃ ረገድ ዘላቂ፣ ዝቅተኛ ካርበን የሚያወጣ እድገት ለማረጋገጥ ያለንን የጋራ አቋም የሚያንፀባርቅ ነው ብለዋል።

 

ከሲንጋፖር ጋር ይኽን የወዳጅነት እና የትብብር ጉዞ በጋራ በመቀጠላችንም ክብር ይሰማናል ነው ያሉት። በላቀ ተግባራዊ ትብብር ንግድ እና ኢንቨስትመንትን በማስፋፋት፣ ዘመናዊ ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስን በማልማት፣ በዲጂታል መሠረተ ልማት፣ በገንዘብ ልውውጥ ቴክኖሎጂ፣ ሳይበር ደኅንነት እና ሰው ሠራሽ አስተውሎት ያለንን ትብብር ለመጠቀም እጅግ ሰፊ አቅም አለን ብለዋል በመልዕክታቸው።

 

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

👇👇👇

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

 

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበሥርዓተ ምግብ ትግበራ የተሻሉ መንደሮችን የመፍጠር ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል።
Next articleሠራዊቱን በአካል እና በሥነ ልቦና በመገንባት በኩል በትኩረት እየተሠራ ነው።