
ባሕር ዳር: ኅዳር 14/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከኔዘርላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዲክ ሾፍ ጋር ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት ከኔዘርላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዲክ ሾፍ ጋር በነበረን ውይይት በኢትዮጵያ እና ኔዘርላንድ መካከል ያለውን ጠንካራ ትስስር ለማጠናከር ውይይት አድርገን ነበር ነው ያሉት።
ከኢትዮጵያ የውጭ ንግድ ቁልፍ መዳረሻዎች አንዷ የሆነችው ኔዘርላንድ ኢንቨስትመንት እና የኢኮኖሚ ትብብር ለማድረግ ጉልህ አቅም አላት ብለዋል።
የአየር ንብረት ለውጥ ጥበቃ ሥራ ትብብርን አስመልክቶም እድሎቻችንን ለመመልከትና የሁለትዮሽ ግንኙነታችንን በጉብኝቶች እና የልውውጥ መርሃ ግብሮች እንድንከውን በውይይቱ ሀሳብ አንስቻለሁ።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
