
ባሕር ዳር: ኅዳር 14/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከብራዚል ፕሬዝደንት ሉዊዝ ኢናችዮ ሉላ ደ ሲልቫ ጋር ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት ከብራዚል ፕሬዝደንት ሉዊዝ ኢናችዮ ሉላ ደ ሲልቫ ጋር ጥሩ ውይይት አድርገናል ብለዋል።
ውይይታችን በኢኮኖሚ እና ዘላቂ የመሠረተ ልማት ጉዳዮች ላይ አተኩረን የሁለትዮሽ ግንኙነታችንን የምናጠናክርባቸውን እድሎች አስመልክቶ የተካሄደ ነበር ነው ያሉት።
ብራዚል በቅርቡ የተካሄደው የCOP30 አስተናጋጅ ሀገር እንደመሆኗ COP32ን በኢትዮጵያ ስናዘጋጅ ከብራዚል የምንወስደው ብዙ ጠቃሚ ልምዶች አሉ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዓለም የአየር ንብረት ጥበቃ ሥራን የሚያራምድ በሚገባ የተሰናዳ መስተንግዶ እንዲኖረን ከልምዶች የተገኙ ሃሳቦችን መለዋወጡን አጠናክረን ለመቀጠል አቅደናል ብለዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
