ወሳኝ የኢኮኖሚ ሪፎርም ሥራዎች የኢትዮጵያን ተወዳዳሪነት ከፍ አድርገዋል።

1
ባሕር ዳር: ኅዳር 14/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከቡድን 20 አባል ሀገራት ጉባኤ ጎን በተካሄደው ኮምፓክት ዊዝ አፍሪካ ( Compact with Africa) መርሐ ግብር ላይ ተካፍለዋል።
መርሐ ግብሩ ሥራው የደረሰበትን ደረጃ በመገምገም የወደፊት ትልሙን መመልከት ላይ ያተኮረ ነበር።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በንግግራቸው የማክሮ ኢኮኖሚ መረጋጋት ሥራዎችን፣ እንደ ገበያን ክፍት የማድረግ ተግባራት፣ የቁጥጥር ማዕቀፎች የማጠናከር ሥራዎች፣ የካፒታል ገበያዎችን የማበርታት እንቅስቃሴዎች ያሉ የኢትዮጵያን ወሳኝ የኢኮኖሚ ሪፎርም ሥራዎችን አንስተዋል።
የረጅም ጊዜ የግል ኢንቨስትመንትን በመሳብ የኢትዮጵያን ተወዳዳሪነት ከፍ ለማድረግ እንዳስቻሉ ገልጸዋል።
መርሐ ግብሩ የአፍሪካን ብሎም የሰፊውን ዓለም የጋራ ብልጽግና በማሳደግ ረገድ ከፍ ያለ ርዕይ ሊይዝ እንደሚገባ ጥሪ በማስተላለፍ መጠናቀቁን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከተመድ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ጋር ተወያዩ።
Next articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከካፍ ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ሞትሲፒ (ዶ.ር) ጋር ተወያዩ።