
ባሕር ዳር: ኅዳር 14/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከተመድ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ጋር ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት ከቡድን 20 ጉባኤ ጎን ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ጋር ውይይት አድርገናል ብለዋል።
ውይይታችን የባለብዙ ወገን ግንኙነታችንን ለማጠናከር ብሎም እንደ የአየር ንብረት ጥበቃ ሥራ፣ ሰላም እና ፀጥታ፣ ዘላቂ ልማት ያሉ የጋራ ዓለም አቀፋዊ ትኩረታችንን በምናጠናክርበት መንገድ ላይ ያጠነጠነ ነበር።
ኢትዮጵያ የCOP32 አስተናጋጅ ሀገር እንደመሆኗ መጠን ሊደረግ ስለሚችለው ድጋፍም ተወያይተናል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
