“የኢትዮጵያ እና ማሌዢያ ግንኙነት ከንግድ ባለፈ ትርጉም ወዳለው ትብብር ተሸጋግሯል” ፕሬዝዳንት ታየ አጽቀሥላሴ 

3

አዲስ አበባ: ኅዳር 10/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የኢፌዴሪ ፕሬዝደንት ታየ አጽቀሥላሴ ይህንን ያሉት በኢትዮጵያ ማሌዥያ ከፍተኛ የቢዝነስ ፎረም ላይ ነው።

 

የማሊያዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር ኢብራሒም ወደ አዲስ አበባ መምጣት የሁለቱን ሀገራት ከንግድ ባለፈ ወደ ሕዝብ ለሕዝብ ትብብር ከፍ እንደሚያደርገው ተናግረዋል።

 

በ1965 የጀመረው የሁለቱ ሀገራት ግንኙነትም ዛሬ በበለጠ እና ትርጉም ሊሰጥ ወደሚችል ምዕራፍ ተሸጋግሯል ብለዋል።

 

ፕሬዝዳንቱ ኢትዮጵያ ከማሊዢያ ጋር ያላት ግንኙነት ትልቅ መኾኑን በመጥቀስ ባለፈው ዓመት ብቻ 1 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ዋጋ ያለው የምግብ ዘይት ኢትዮጵያ ከሀገሪቱ አስገብታለች ብለዋል።

 

ኢትዮጵያ ፖሊሲዋን በማሻሸል የፋይናንስ ሥርዓቱን ዲጂታላይዝ ማድረግ እንደቻለችም ጠቅሰዋል።

 

የግብርና ዘርፉን ከጥገኝነት ማላቀቅ መቻሉንም ጠቅሰዋል። ሀገሪቱ የፖሊሲ ማሻሸዎችን በማድረግ የኢንቨስትመንት ሥነ ምህዳር መፍጠሯን ጠቅሰው ማሊዢያውያን በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርጉም ፕሬዝዳንቱ ጥሪ አቅርበዋል።

 

ዘጋቢ፦ አንዱ ዓለም መናን

 

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

👇👇👇

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

 

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleኢትዮጵያ የቀጣናው የኃይል ማዕከል ለመኾን እያደረገች ያለውን ጥረት የማሊዥያው ጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር ኢብራሒም አደነቁ።
Next articleበክልሉ የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ላይ የተሠማሩ የግል ሥራ እና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች አሉ።