
አዲስ አበባ: ኅዳር 10/2018 ዓ.ም (አሚኮ)
በሰመራ ሎጊያ ከተማ ሲካሄድ የሰነበተው 10ኛው የከተሞች ፎረም የማጠቃለያ መርሐ ግብር ተካሂዷል።
በማጠቃለያ መርሐ ግብሩ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ አትዮጵያ ቀደም ያለ የከተሜነት ታሪክ ያላት ቢኾንም በዘላቂ ስትራቴጅ አለመመራታቸው እና በመሠረተ ልማት አለመተሳሰራቸው ከተሞች ዕድሜያቸውን የሚመጥን ዕድገት ሳያስመዘግቡ ቆይተዋል ብለዋል።
ከታሪክ በመማር የኢትዮጵያን ዕድገት የሚመጥን የከተማ ልማት ለመገንባት መንግሥት ትኩረት መስጠቱንም አንስተዋል።
ከተሞች የዕድገት ማዕከል እንዲኾኑ እና ለነዋሪዎች ምቹ ለማድረግ መንግሥት በትኩረት እየሠራ ሰለመኾኑም ተናግረዋል።
የመኖሪያ ቤት እጥረትን በማቃለል ዜጎች የመኖሪያ ቤት ባለቤት እንዲኾኑ ማስቻል አለያም በዝቅተኛ ኪራይ መኖሪያ እንዲያገኙ ማድረግ ላይ መንግሥት ትኩረት የሰጠበት ዘርፍ መኾኑን አስረድተዋል።
ከተሞችን ውብ እና ጽዱ ብሎም ባሕላዊ እና ሃይማኖታዊ ሃብቶችን የቱሪስት መዳረሻ በማድረግ የከተማ ነዋሪውን የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚገባም ነው ያስገነዘቡት።
ዘጋቢ፦ ተመስገን ዳረጎት
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
