መሶብ የአንድ አገልግሎት ማዕከል ዜጎች ክብራቸው ተጠብቆ እና ሳይንገላቱ ተጠቃሚ እንዲኾኑ የሚያስችል ነው።

2
አዲስ አበባ: ኅዳር 08/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ከ10ኛው የከተሞች ፎረም ጎን ለጎን የተለያዩ ሁነቶች በሰመራ ሎጊያ ከተማ እየተከናወኑ ይገኛሉ። ዛሬ በሰመራ ሎጊያ ከተማ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ሥራ ጀምሯል።
በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የፋይዳ መታወቂያ፣ የንግድ ፈቃድ፣ የገቢዎች አገልግሎት፣ የቴሌኮም እና ሌሎች አገልግሎቶች እንደሚሰጡ ተገልጿል።
የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር መኩሪያ ኃይሌ (ዶ.ር) መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በተቋማት የሚስተዋለውን የተጓተተ አገልግሎት ለማቀላጠፍ የሚያስችል መኾኑን ተናግረዋል።
የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስትሯ ጫልቱ ሳኒ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የዜጎችን የአገልግሎት አሰጣጥ እርካታ እንዲያገኙ የሚያስችል ነው ብለዋል።
የተደራጀ እና በአንድ ቦታ የመሶብ አገልግሎት መሠጠቱ ዜጎች ክብራቸው ተጠብቆ እና ሳይንገላቱ በጽዱ አካባቢ የአገልግሎት ተጠቃሚ እንዲኾኑ የሚያስችል መኾኑን አንስተዋል።
እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በሀገሪቱ ሁሉም አካባቢዎች በከንቲባ በሚመሩ ከተሞች ተደራሽ ለማድረግ እየተሠራ መኾኑ ተገልጿል።
ዘጋቢ:- ተመስገን ዳርጎት
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየተዘረጋው አሠራር ፈጣን እና ዘመናዊ በመኾኑ የመንግሥት አገልግሎቱን በቀላሉ ለማግኘት ያስችላል።
Next articleብዙዎች ተስፋ ያደረጉበት የቡሬ ደብረ ማርቆስ ሳብስቴሽን ግንባታ ምን ላይ ነው?