የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ኅብረ ብሔራዊ አንድነት የሚጠናከርበት ነው።

4
አዲስ አበባ: ኅዳር 02/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሆሳዕና ከተማ ይከበራል።
በዓሉ “ዴሞክራሲያዊ መግባባት ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ መልዕክት እንደሚከበር ተገልጿል።
የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር ኅዳር 29/2018ዓ.ም የሚከበረው የዘንድሮ የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ኢትዮጵያ በብዙ ስኬቶች ውስጥ ኾና የምታከብረው እና እስከዛሬ ከነበሩት በተለየ ትልቅ ትርጉም የሚሰጠው ነው ብለዋል።
የሕዳሴ ግድቡ የተጠናቀቀበት ፣ የነበረውን የኢኮኖሚ ስብራት የሚጠግን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ የተደረገበት ስኬታማ ዓመት መኾኑን ገልጸዋል። ከፊታችን የምናካሄደውን ሀገር አቀፍ ምርጫ ጨምሮ የጋራ ምክር ቤቶቹን የሥራ ዘመናቸውን ጨርሰው እንደ አዲስ የሚዋቀሩበት በመኾኑ ብዙ ሥራ ይጠብቀናል ብለዋል።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሚከበረው የብሔር ብሔረሰቦች ቀንም ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን በማጠናከር ዜጎች ማንነታቸውን እና ባሕላቸውን የሚያሳዩበት ትልቅ መድረክ መኾኑንም ተናግረዋል።
20ኛውን የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በዓል በድምቀት እና በልዩ ሁኔታ ለማክበርም በቂ ዝግጅት መደረጉን አስታውቀዋል።
ዘጋቢ:- ቤተልሄም ሰለሞን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
Previous article10ኛው የከተሞች ፎረም የቅድመ ዝግጁት ሥራ መጠናቀቁን የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስትቴር አስታወቀ።
Next articleየኢትዮጵያ ንግድ ባንክ “ሲቢኢ በጄ ” የተሰኘ አዲስ የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎት ይፋ አደረገ።