ዘላቂ ሰላምን ለማጽናት የወጣቶች እና ሴቶች ተሳትፎ ጉልህ መኾኑ ተገለጸ።

19
ባሕር ዳር: ጥቅምት 21/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የባሕርዳር ከተማ አሥተዳደር “ዘላቂ ሰላም ለማጽናት የወጣቶችና ሴቶች ተሳትፎ ጉልህ ነው” በሚል መሪ መልዕክት እየመከረ ነው።
በመድረኩ የመወያያ ሰነድ የቀረበ ሲኾን በቀረበው ሰነድ ላይ ውይይት ተደርጎበታል።
በውይይቱ የውጭ ሴራዎችን በማምከን አንፀባራቂ ድሎችን ማስመዝገብ እንደሚገባ የምክክሩ ተሳታፊዎች ገልጸዋል።
በመድረኩ የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት መምሪያ ኀላፊ ቶማስ ታምሩ እንዳሉት በሀገር ላይ የተፈጠሩትን ዘርፈ ብዙ ጥቃቶችን ቅዥት በማድረግ እንደ ሀገር ከታሰበበት ግብ ላይ ለመድረስ በርካታ ሥራዎች ተሠርተዋል።
ይህንን ሥራ አጠናክሮ ውጤታማ ለማድረግ የወጣቱ እና የሴቶች ሚና ከፍተኛ እንደነበር ነው ያብራሩት።
ኢትዮጵያ አሁን ላይ እያስመዘገበችው ካለው የልማት እና የመልካም አሥተዳደር ውጤቶች አንፃር ተወስዶ ሲታይ ብዙ ሥራ መሠራቱን ጠቁመዋል።
በሌላ በኩል የሀገርን ልማት ለማደናቀፍ ጥረት የሚያደርጉ አካላት እንዳሉም ተናግረዋል።
በቀጣይም ችግሮችን በመቅረፍ የውጭ ሴረኞችን አንገት ሊያስደፋ የሚችል ሥራ በቅንጅት መሥራት እንደሚጠበቅም አስገንዝበዋል።
ለዚህ ደግሞ የወጣቱ እና የሴቶች ሚና ከፍተኛ በመኾኑ ሁሉም የበኩሉን በመወጣት ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ርብርብ ማድረግ ይገባዋል ነው ያሉ።
ዘጋቢ፦ሰናይት በየነ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየቅጥር ማስታወቂያ
Next articleሕገ ወጥ የመሬት ወረራን ለመከላከል እየተሠራ ነው።