የማዳበሪያ ፋብሪካው ሲጠናቀቅ በዓመት 30 ሚሊዮን ኩንታል የዩሪያ ማዳበሪያ የማምረት አቅም አለው።

10
ባሕር ዳር: ጥቅምት 18/2018 ዓ.ም (አሚኮ) 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤ እየተካሄደ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ እየሰጡ ነው።
ማብራሪያ ከሰጡባቸው ጉዳዮች ውስጥ መንግሥት ዳንጎቴ ከተባለ የውጭ ድርጅት ጋር በመተባበር የሚያለማው የማዳበሪያ ፋብሪካ አንዱ ነው።
ፋብሪካው በዓመት 30 ሚሊዮን ኩንታል የዩሪያ ማዳበሪያ የማምረት አቅም እንዳለውም ገልጸዋል።
ፕሮጀክቱ ማዳበሪያን ከማምረት ባለፈ የሚመረተው ማዳበሪያ የአካባቢውን አፈር፣ የምርቱን አይነት እና ምጥጥኑን መሠረት ያደረገ እንዲኾን እየተሠራ መኾኑንም አብራርተዋል።
እያንዳንዱ የማዳበሪያ ምርት ባርኮድ ተሠጥቶት እና መዳረሻው ታውቆ እንዲሠራጭም ትኩረት ተደርጓል ብለዋል።
ማዳበሪያን በረከሰ ዋጋ አርሶ አደሩ ድረስ ማድረስ ሌላኛው ትኩረት እንደኾነም ገልጸዋል።
ከማዳበሪያ ማምረት ባለፈ 1ሺህ ሜጋ ዋት ኀይል ማመንጨት፣ የነዳጅ ማጣሪያን (ሪፋይነሪ) ጨምሮ ሌሎች መሠረተ ልማቶችን ለማጠናቀቅ 10 ቢሊዮን ዶላር በጀት መመደቡን ገልጸዋል።
ፕሮጀክቶቹ በተቀመጠላቸው ጊዜ እንደሚጠናቀቁም ጠቁመዋል።
በዳግማዊ ተሠራ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article“ለክብራችን ስንል ተረጅነትን ማስቆም አለብን” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)
Next article“አሁንም ለሰላማዊ ትግል በራችን ክፍት ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)