በኢትዮጵያ የተጀመረው የጋዝ ፕሮጀክት ከውጭ የሚገባ ምርትን በመተካት ከፍተኛ ሃብትን ማዳን የሚያስችል ነው።

4
ባሕር ዳር: ጥቅምት 17/2018 ዓ.ም (አሚኮ) 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤ እየተካሄደ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል። ማብራሪያ ከሰጡባቸው ጉዳዮች የጋዝ ፕሮጀክት አንዱ ነው።
በኢትዮጵያ ሶማሊ ክልል በአንድ ቦታ ብቻ 21 ትሪሊዮን ኪዩቢክ ፊት የጋዝ ክምችት እና ድፍድፍ ነዳጅ ክምችት እንዳለ በሦሥተኛ ወገን መረጋገጡን ገልጸዋል።
ይሁን እንጅ ትክክለኛ አልሚ ባለሃብቶችን ለይቶ ወደ ልማት የማስገባት ችግሮች እንደነበሩ ነው የተናገሩት።
ከሁለት ዓመት በፊት የጋዝ ፕሮጀክት ልማት ለቻይና አልሚ ድርጅት ተሰጥቶ የመጀመሪያውን ምዕራፍ ማጠናቀቅ መቻሉን ገልጸዋል።
ሁለተኛው ምዕራፍ በቅርቡ የተጀመረ ሲኾን በ24 ወራት ውስጥ እንደሚጠናቀቅም ገልጸዋል።
ከዚህ በተጨማሪ 1ሺህ ሜጋ ዋት ኀይል ለማጠናቀቅም እየተሠራ መኾኑን አብራርተዋል።
ኢትዮጵያ ለነዳጅ እና ለማዳበሪያ ከፍተኛ ወጭ እንደምታወጣ ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ የተጀመሩት የጋዝ እና የማጣሪያ ፕሮጀክቶች ሲጠናቀቁ የውጭ ምርቶችን በመተካት ከፍተኛ ሃብትን ማዳን እንደሚቻልም ገልጸዋል።
በዳግማዊ ተሠራ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article“ለውጡ ከታሰበው እና ከታለመው ባሻገር የተሳካ ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)
Next article“በቢሾፍቱ የሚገነባው ኤርፖርት ኢትዮጵያ አፍሪካን ከመላው ዓለም ጋር የምታገናኝበት ይኾናል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)