
ባሕር ዳር: ጥቅምት 18/2018 ዓ.ም (አሚኮ) 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ5ኛ ዓመት የሥራ ዘመኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በተገኙበት 2ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ይገኛል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያ እየሰጡ ነው።
የግብርናው ዘርፍ ባለፈው ዓመት 7 ነጥብ 3 በመቶ እድገት ማምጣቱን ገልጸዋል። በለውጡ ማግስት የኢትዮጵያ የሩዝ ምርት 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል ነበር ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለፈው ዓመት 63 ሚሊዮን ኩንታል የሩዝ ምርት አምርተናል ብለዋል።
በለውጡ ማግስት ኢትዮጵያ 47 ሚሊዮን ኩንታል የስንዴ ምርት ታመርት ነበር፤ ከውጭም በቢሊዮን ዶላር በሚገመት ገንዘብ ስንዴ ታስገባ ነበር ነው ያሉት። ባለፈው ዓመት 280 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ስንዴ አምርተናል ብለዋል። ይህም የኢትዮጵያን እድገት ያሳያል ነው ያሉት።
ከለውጡ ማግስት 4 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል ቡና አምርተናል። ይህም በዘመኑ ትልቁ ነበር ሲሉ ገልጸዋል። ባለፈው ዓመት ደግሞ 11 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል ቡና አምርተናል። ግብርና ላይ የመጣው ለውጥ ግብርና መር ከተባለበት ዘመን የሚበልጥ ነው ብለዋል።
“ግብርና ላይ እምርታ አምጥተናል ነው ያሉት” ግብርና ላይ ለውጥ እንዲመጣ ላደረጉም ምስጋና አቅርበዋል።
ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
