በአረንጓዴ አሻራ አማካኝነት 48 ቢሊዮን ችግኞችን መትከል ተችሏል።

1
ባሕር ዳር: ጥቅምት 18/2018 ዓ.ም (አሚኮ) 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በተገኙበት 2ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ይገኛል።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ላነሷቸው ጥያቄዎችም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ምላሽ እየሰጡ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመግቢያቸው 2017 በጀት ዓመት በኢትዮጵያ ታሪክና የታሪክ እጥፋት ትላልቅ ጉዳዮች የተሳኩበት፣ ይቻላሉ ተብለው የማይታሰቡ ጉዳዮች የተቻሉበት መሆኑንም ለምክር ቤቱ ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከግብርና መር ወደ ብዝሃ ዘርፍ እንዲሸጋገር የተነደፈው ፖሊሲ በእጅጉ ውጤታማ መኾኑን አብራርተዋል።
ከለውጡ ወዲህ መንግሥት ከሕዝብ ጋር ተሳስሮ ልማት እንዲያመጣ ግልጽ አቅጣጫ በመቀመጡ መንግሥትና ሕዝብ ተሳስረው በአረንጓዴ አሻራ አማካኝነት 48 ቢሊዮን ችግኞችን መትከል ችለዋል ብለዋል።
ለዚህ ስኬት ደግሞ ከ25 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያዊያን ሳይታክቱ በነጻ በየዓመቱ ወጥተው ችግኞችን መትከል ችለዋል ነው ያሉት። ይህም የመንግሥትና ሕዝብ ቅንጅትን በተግባር ያሳየ ነው ብለዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleለረጅም ጊዜ የቆዩ ፕሮጄክቶች እንዲጠናቀቁ ምን እየተሠራ ነው?
Next article“በግብርናው ዘርፍ እምርታ አምጥተናል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)